Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከቱርኩ የመከላከያ ሚኒስትር ሁሉሲ አካር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 2 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከቱርኩ የመከላከያ ሚኒስትር ሁሉሲ አካር ጋር ተወያዩ።
በፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የተመራ ልዑክ የቱርክ መንግስት ባዘጋጀው የEFES 2022 ወታደራዊ ልምምድ ላይ ለመሳተፍ ትናንት ቱርክ መግባቱ ይታወሳል።
ከልምምዱ ጎን ለጎንም ከቱርክ መከላከያ ሚኒስትር ጋር ሃገራቱ በወታደራዊ ዘርፍ በትብብር መስራት በሚችሉበት አግባብ ላይ መወያየታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከቱርክ አቻቸው ጄነራል ያሳር ጉለር ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያም መክረዋል፡፡
Exit mobile version