Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኤስኦኤስ የሕጻናት መንደር በጦርነቱ ለተጎዱ አካባቢዎች በ145 ሚሊየን ብር የልማት ፕሮጀክት ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኤስኦኤስ የሕጻናት መንደር 145 ሚሊየን ብር በመመደብ በጦርነቱ ለተጎዱ 130 ሺህ የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ የሚኾን የልማት ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል።

ፕሮጀክቱ በጦርነቱ ምክንያት ዘረፋና ውድመት ለደረሰባቸው አካባቢዎች የሚውል ነው ተብሏል።

ሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ ዞንና የዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች እንደሚኾኑ መገለጹን አሚኮ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

Exit mobile version