አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደሴ ከተማ ከጦርነቱ በኋላ ከ18 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ 75 ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መሰጠቱን የከተማ አስተዳደሩ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ገለጸ፡፡
በደሴ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ የተዘጋጀ የባለሃብቶች እና የባለድርሻ አካላት የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የተገኙት የደሴ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ሃላፊ አቶ አለባቸው ሰይድ እንደገለጹት÷ ባለሃብቶቹ ከ18 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል አስመዝግበዋል፡፡
ኢንቨስትመንቶቹ ወደ ስራ ሲገቡ ከ92 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል እንደሚፈጥሩ ነው ሃላፊው የተናገሩት፡፡
የደሴ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ በበኩላቸው÷ፈጥኖ ወደ ስራ በመግባት በኩል ዘርፈ ብዙ ችግሮች በመኖራቸው ባለሃብቶች፣ መንግስት፣ የልማትና አበዳሪ ተቋማት ችግሩን ለመፍታት ውይይት እንዳስፈለገ አንስተዋል፡፡
በቀጣዩ ዓመት ታጥረው የሚቀመጡና ምርት የማይጀምሩ ኢንዱስትሪና አምራቾች ሊኖሩ አይገባም ያሉት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው÷በሁሉም ዘርፍ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት መነጋገር አስፈላጊ ነው ብለዋል።
በአንድነት ናሁሰናይ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!