Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ግቢ እየተተገበረ ያለውን የተቀናጀ የከተማ ግብርና እንቅስቃሴ ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ግቢ እየተተገበረ ያለውን የተቀናጀ የከተማ ግብርና እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በጉብኝታቸው ወቅት እንደገለጹት÷ የከተማ ግብርና በከተማ አስተዳደሩ ትኩረት ተሰጥቶት በግለሰቦች መኖሪያ ግቢ፣ በመንግሥት ተቋማት በሚገኝ ክፍት ቦታ እና ክፍት መሬት በተገኘበት ሥፍራ ሁሉ በንቅናቄ መልክ ተጀምሮ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች እየደጎመ ነው፡፡
በዚህም ትኩስ የአትክልት ውጤቶችን ለተጠቃሚ በማድረስ ተጨባጭ ውጤት እያመጣ መሆኑን ገልጸው÷ ይህንም በየአካባቢው እየተመለከትን ነው ብለዋል።
ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ግቢ የተመለከትነው የግብርና ሥራ በአጭር ጊዜና በጠባብ መሬት የተቀናጀ የከተማ ግብርናን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚቻል ማስረጃ ነው ማታቸውን ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያላክታል፡፡
በዚህ ጠባብ ቦታ የንብ ማነብ ሥራ፣ የአሳ እርባታና ሌሎችም በአጭር ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውሉ የጓሮ አትክልቶችን ማልማት መቻሉም ለሁሉም ትምህርት ይሰጣል ነው ያሉት፡፡
በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች እፎይታን መፍጠር የሚችል በመሆኑ ሁሉም ትኩረት እንዲሰጠው አሳስበዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version