የሀገር ውስጥ ዜና

1ሺህ 85 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By Mikias Ayele

June 03, 2022

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት በተካሄዱ ሦስት በረራዎች 1ሺህ 85 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

ከተመለሱት ውስጥ ሁለቱ ሕጻናት ሲሆኑ 1 ሺህ 83ቱ ደግሞ ወንዶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማዕከላት እንዲሄዱ መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

እስካሁን ድረስ በተከናወነ ዜጎችን የመመለስ ሥራ ከ32 ሺህ 321 በላይ ኢትዮጵያውያን መመለሳቸውም ነው የተገለጸው፡፡