ቴክ

ቻይና 9 የመገናኛ ሳተላይቶችን ወደ ህዋ አመጠቀች

By Mikias Ayele

June 03, 2022

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ሰው ሰራሽ መረጃ ሰብሳቢ ተሽከርካሪዎቿ መረጃ እንዲያገኙ ያስችላሉ ያለቻቸውን ዘጠኝ ሳተላይቶች ወደ ህዋ ልካለች፡፡

ሳተላይቶቹ በደቡብ ምዕራብ ቻይና ሲቹዋን ግዛት ከሚገኘው ዚቻንግ  የሳተላይት ማምጠቂያ ማዕከል ሎንግ ማርች 2 ሲ በተሰኘ ሮኬት በተሳካ ሁኔታ ወደ ህዋ መላካቸው ተገልጿል፡፡

ሳተላይቶቹ በቤጂንግ ሰዓት አቆጣጠር 12 ሰዓት ላይ የተነሱ ሲሆን÷ ወደ ምህዋር መግባታቸውም ተመላክቷል፡፡

የተላኩት ሳተላይቶች ሰው ሰራሽ መረጃ ሰብሳቢ ተሸከርካሪዎች እና የሞባይል ስልኮች ከሳተላይት ጋር መስተጋብር እንዲኖራቸው ከማድረግ ባለፈ ለባህር ጥናት እና አካባቢ ጥበቃ መረጃ ይሰጣሉ ተብሏል፡፡

በቻይና የተሸከርካሪ ቴክኖሎጂ አካዳሚ የተዘጋጀው የሎንግ ማርች 2ሲ ሮኬት በዘንድሮው አመት ለአራት ተከታታይ ጊዜ ሳተላይት ማምጠቅ መቻሉን ሲ ጅ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡

ሎንግ ማርች- 2ሲ ሮኬት በአንድ ተልዕኮ ብዙ ሳተላይቶችን በመላክ አዲስ ክብረ ወሰን ማስመዝገብ መቻሉን ተመላክቷል፡፡