Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያ የዓመቱ ምርጥ የመካነ ቅርስ ስፍራዎች መዳረሻ ሀገር በመሆን የፓትዋ ሽልማትን አሸነፈች

Ancient obelisks in city Aksum, Ethiopia. UNESCO World Heritage site. African culture and history place

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ የአመቱ ምርጥ የቅድመ ታሪክ ቅሪተ አካልና መካነ ቅርስ ሥፍራዎች መዳረሻ ሀገር በሚል በጀርመን በየአመቱ በሚካሄደው የፓትዋ ሽልማት አሸናፊ ሆነች።

የፓሲፊክ አካባቢ ተጓዦች ማህበር (ፓትዋ) ሽልማት በየአመቱ በጀርመን በሚካሄደው የበርሊን የዓለም የቱሪዝም ንግድ ትርዒት ላይ የሚሰጥ የእውቅና ስነ ስርዓት ነው።

በዘንድሮው የፓትዋ ሽልማት በተለያዩ ዘርፎች 13 የዓለም ሀገራት አሸናፊ መሆናቸውን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያም የቅድመ ታሪክ ቅሪተ አካልና መካነ ቅርስ ሥፍራዎች መዳረሻ ሀገር በሚለው ዘርፍ በቀዳሚነት አሸንፋለች።

በሌላ በኩል የኢፌዴሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው ከሰሃራ በታች ምርጥ የቱሪዝም ሚኒስትር በሚል ተመርጠዋል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

Exit mobile version