አዲስ አበባ፣ግንቦት 23፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በወላይታ ዞን በገሱባ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሁለት ጥርስ ያበቀለ ሕፃን መወለዱን ሆስፒታሉ አስታውቋል፡፡
የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ፀጋዬ እንድሪያስ እንደገለጹት ÷ ትናንት ሁለት ጥርስ ያለው ልጅ የተወለደ ሲሆን ይህ ክስተትም ከሚወለዱ 2 ሺህ ወይም 3 ሺህ ሕፃናት በአንዱ ላይ ሊከሰት እንደሚችል ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡
ይህም ክስተት በህክምና አጠራሩ የሕፃናት የወሊድ ጊዜ ጥርስ (Natal teeth) ተብሎ እንደሚጠራም የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ መናገራቸውን ከገሱባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ዶክተሩ አያይዘውም ሁለት ጥርስ በማብቀል የተወለደው ሕፃን ምንም ሳይቸገር ጡት እየጠባ መሆኑን እና በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡