Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከዋልያዎቹ ስብስብ አምስት ተጫዋቾችን ቀነሱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከዋልያዎቹ ስብስብ አምስት ተጨዋቾችን መቀነሳቸው ታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታውን ከማላዊ እና ግብፅ ጋር ለማድረግ አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ከጠሯቸው 28 ተጨዋቾች አምስት ተጨዋቾችን መቀነሳቸው ታውቋል፡፡
አሰልጣኙ ከሌሴቶ ብሔራዊ ቡድን ጋር ካደረጉት ሁለት የአቋም መፈተሻ ጨዋታ በኋላ ነው ተጫዋቾችን ከብሄራዊ ቡድኑ የቀነሱት፡፡
በዚህም የመከላከያውን አማካይ ቢኒያም በላይ ፣ የሐዋሳ ከተማውን አማካይ ወንድማገኝ ኃይሉ ፣ የወልቂጤ ከተማውን ግብ ጠባቂ ሰዒድ ሀብታሙ፣ የሀዲያ ሆሳዕናው ተከላካይ ብርሀኑ በቀለ እና አጥቂውን ሀብታሙ ታደሰ መቀነሳቸውን የሶከር ኢትዮጵያ ዘገባ ያመላክታል።
Exit mobile version