የሀገር ውስጥ ዜና

ሀገራዊ ቴክኖሎጂን በአግባቡ መጠቀምና ማልማት ላይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ተመላከተ

By Shambel Mihret

May 27, 2022

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገራዊ የቴክኖሎጂ ፍላጎትን መለየት፣ መምረጥ፣ መጠቀም፣ ማልማት እና የአገልግሎት ጊዜያቸው ሲያበቃ ማስወገድ ላይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ተመላከተ፡፡

በአገር በቀል ቴክኖሎጂ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግርና ሀገራዊ የሳይንስ ቴክኖሎጂ እንዲሁም ኢኖቬሽን ፖሊሲ አስተዳደርን የተመለከተ ዛሬ ዓውደ ጥናት ተካሂዷል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ በአውደ ጥናቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የቴክኖሎጂ መረጃዎችን በተለያዩ ዘርፎች በማሰባሰብ፣ በመመዝገብና በመተንተን ለቀጣይ ስራ ግብዓት ሆኖ እንዲያገለግል ሀገራዊ የቴክኖሎጂ መረጃ ስርዓት በጋራ ለመፍጠር ይሰራል ብለዋል።

በመድረኩ የዘርፉን የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች የተመለከቱ ርዕሰ ጉዳዮች በተሳታፊዎች ቀርበው ውይይት መደረጉን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  መረጃ ያመላክታል፡፡

በዓውደ ጥናቱ የከፍተኛ ትምህርት የምርምር ተቋማት ኃላፊዎች፣ የግሉ ዘርፍ ባለሀብቶች፣ የሀገር በቀል የፈጠራ ባለቤቶችና ኢንቨስተሮች፣ የፌደራልና የክልል መንግስት ተቋማት ኃላፊዎች እንዲሁም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች ተሳትፈዋል።