የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያና እና ኢኳቶሪያል ጊኒ በማዕድንና ኢንቨስትመንት ዘርፍ በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ

By Feven Bishaw

May 26, 2022

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና እና ኢኳቶሪያል ጊኒ በማዕድንና ኢንቨስትመንት ዘርፍ በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት መካሄዱን የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ገለፁ ፡፡

የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷ከኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ጋር በመሆን ከኢኳቶሪያል ጊኒ የማዕድንና ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስትር ጋር በማዕድን ኢንቨስትመንትና ንግድ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውን ገልጸዋል።