አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የወንዶች ፕሪሚየር ሊግ በወላይታ ዲቻ የእግር ኳስ ቡድን አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
የ2014 ዓ.ም የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የወንዶች ፕሪሚየር ሊግ በወላይታ ዲቻ የእግር ኳስ ቡድን አሸናፊነት ሲጠናቀቅ፥ ሀዋሳ ከተማ እና አርባ ምንጭ ከተማ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል፡፡
የውድድሩን አጠቃላይ አሸናፊ ለመለየት በተካሄደ የፍፃሜ ጨዋታ ወላይታ ዲቻ ሀዋሳ ከተማን 2 ለ 0 በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት መሆኑን የእግርኳስ ፌደሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡