ስፓርት

በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸነፈ

By Meseret Awoke

May 22, 2022

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ25ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ ቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በባህር ዳር ስታዲየም በተደረገው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ኦኪኪ ኦፎላቢ በ3ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠራት ግብ ፋሲል ከነማ ወሳኝ 3 ነጥብ ማግኘት ችሏል፡፡

አፄዎቹ ዛሬ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ፋሲል ከነማ በ49 ነጥብ ከፕሪምየር ሊጉ መሪ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ወደ 5 ማጥበብ ችለዋል፡፡

በአንፃሩ ፈረሰኞቹ ከ24 ጨዋታዎች በኋላ የመጀመሪያ ሽንፈታቸውን ሲያስተናግዱ፥ ከ8 ጨዋታዎች በኋላም የመጀመሪያ ግብ ተቆጥሮባቸዋል፡፡

ረፋድ ላይ የተደረገው የወላይታ ዲቻ እና የአርባምንጭ ከተማ ጨዋታ ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡