Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

“የሸዋል ኢድ” የሐረሪ ክልል ባለሥልጣናት እና ዳያስፖራዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪዎች ዘንድ በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የሸዋል ኢድ የሐረሪ ክልል ባለሥልጣናት እና ዳያስፖራዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው።

በዓሉ ሃይማኖታዊና ባሕላዊ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ ነው እየተከበረ ያለው።

በበዓሉ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ኦርዲን በድሪ ጨምሮ የተለያዩ ሚኒስትሮች እና የክልሉ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ታላቁን “ከኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት” ጥሪ ተቀብለው ወደ ሀገር ቤት የመጡ ዳያስፓራዎችም በበዓሉ ላይ ተገኝተዋል።

በሐብታሙ ተክለ ስላሴ

Exit mobile version