ቴክ

ፌስቡክ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የዓለም ጤና ድርጅት በገጹ በነጻ እንዲያስተዋውቅ ፈቀደ

By Tibebu Kebede

March 04, 2020

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 25፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ፌስቡክ ኮሮና ቫይረስን ለመዋጋት ከሚደረገው ጥረት ጋር በተያያዘ የዓለም ጤና ድርጅት በገጹ በነጻ እንዲያስተዋውቅ ፈቀደ።

የፌስቡክ ዋና ስራ አስፈጻሚ ማርክ ዙከርበርግ ቫይረሱን በተመለከተ የሚወጡ የተሳሳቱ መረጃዎችን ለማጥራት የዓለም ጤና ድርጅት በነጻ እንዲያስተዋውቅ መፍቀዱን ተናግረዋል።

አያይዘውም ኩባንያው ለተጠቃሚዎቹ ማስታወቂያ ከማቅረብ ባለፈ ሌላ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

የኩባንያው እርምጃ የፌስቡክ ተጠቃሚወች በቀጥታ ከዓለም ጤና ድርጅት እንዲሁም ከየአካባቢው የጤና ድርጅቶች ባለስልጣናት ቫይረሱን በተመለከተ ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ተብሏል።

ፌስቡክ የኮሮና ቫይረስን በተመለከተ የሚወጡ የተሳሳቱ መረጃወችን በመከላከል ትክክለኛ መረጃ ለተጠቃሚዎች በመስጠት ማህበራዊ ሃላፊነቱን እንደሚወጣ ገልጿል።

እስካሁን 93 ሺህ የሚደርሱ ሰወች በቫይረሱ ሲጠቁ፥ ከ3 ሺህ በላይ ሰወች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል።

ምንጭ፦ ሬውተርስ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision