Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሶማሌ ክልል አመራሮች በደጋህሌ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኢንጂነር መሀመድ ሻሌና በክልሉ ምክር ቤት አፈጉ ባኤ ወይዘሮ አያን አብዲ የተመራ የልዑካን ቡድን በደጋህሌ ከተማ የሚገኙ ፋብሪካዎችንና የአትክልትና ፍራፍሬ ማሳዎችን ጎበኘ፡፡
የልዑካን ቡድኑ አባላት በጉብኝታቸው÷ በፉፈን ዞን ሸበሌይ ወረዳ ደጋህሌ ቀበሌ የሚገኘውን የዱቄት ፋብሪካ፣ የሚና ውሃ ፋብሪካ፣ በቀበሌው የሚገኙ የተለያዩ የፍራፍሬ ማሳዎችንና ሌሎች የልማት ስፍራዎችንም ተመልክተዋል።
ኢንጂነር መሀመድ ሻሌ÷ የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች በጉብኝቱ ከተመለከቱት ልማት ልምድ በመቅሰም በክልሉ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ያግዛል ማለታቸውን የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡
አመራሮቹ በየጊዜው በልማቱ ዘርፍ ያሉ ክፍተቶችን የሚመጥን መልስ በመስጠት ከጉብኝቱ በቀሰሙት ልምድ÷ ሁሉም በያለበት በአካባቢው ባለው ምቹ ሁኔታ በመታገዝ ልማትን ለማሳደግ እንዲረባረቡ ጠይቀዋል፡፡
Exit mobile version