አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት በሶስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳዑዲ ዓረቢያ የመመለስ ስራ 1 ሺህ 22 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ተመለሱ፡፡
ከተመላሾች ውስጥም 108 ሴቶች ሲሆኑ ÷ ዘጠኝ ሚሆኑት ደግሞ ህጻናት መሆናቸው ተገልጿል፡፡
ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ መደረጉን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
እስካሁን ድርስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ስራ ቁጥራቸው ከ24 ሺህ 660 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉ ተገልጿል፡፡