አዲስ አበባ፣ግንቦት 4፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በተካሄደ ጨዋታ መሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ ጥሏል፡፡
ፈረሰኞቹ ረፋድ 4 ሰዓት በባህርዳር ስታዲየም ከወላይታ ዲቻ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ያለምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ መጣሉን ተከትሎ የነጥብ ልዩነቱን ለማጥበብ እና ወደ ዋንጫ ፉክክር ለመመለስ የፋሲል ከነማ አሸናፊነት ተጠባቂ ነው፡፡