አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ በወደብ ከተማዋ ማሪፑል ለሶስት ቀናት የሚቆይ ተየኩስ አቁም ልታደርግ መሆኑን አስታውቃለች፡፡
የተኩስ አቁሙ በሩሲያ ሀይሎች ከበባ ውስጥ ከነበረው የአዞቮስታል የብረት ፋብሪካ ንፁህን ዜጎች በሰላም እንዲወጡ ለማድረግ ያለመ መሆኑን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የተኩስ አቁም ስምምነቱ ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀናት የሚቆይ መሆኑም ታውቋል፡፡
ውሳኔው ንፁሀን ዜጎች በሰላም እንዲወጡ የሰብአዊ ኮሪደሮችን እንደሚከፍቱ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ሰርጌይ ሾይጉ መናገራቸውን አር ቲ ዘግቧል፡፡