የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ትናንት ለክርስትና እምነት አባቶች የምሳ ግብዣ አደረጉ

By Meseret Awoke

May 02, 2022

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የትንሣኤን በዓል ምክንያት በማድረግ በትናንትናው ዕለት ለክርስትና እምነት አባቶች የምሳ ግብዣ አድርገዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

ኢትዮጵያ የገጠማትን ፈተና ለመፍታት መንግሥትና የሃይማኖት አባቶች በጋራ እንዴት መሥራት እንዳለባቸው እግረ መንገድ ውይይት መደረጉን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።