Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ግብጽ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነ የምድር ውስጥ የባቡር ጣቢያ አስመረቀች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ግብጽ በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ የመጀመሪያ የሆነ የምድር ውስጥ የባቡር ጣቢያ አስመረቀች፡፡

ፕሮጀክቱ  ሀገሪቱ የባቡር ትራንስፖርት ዘርፍ ለማዘመን የያዘች እቅድ አንዱ አካል ነው ተብሏል፡፡

በትናንናው ዕለት በይፋ የተመረቀው ይህ የመሬት ውስጥ የባቡር ጣቢያ 10 ሺህ ሜትር ስኮየር መሬት ላይ ያረፈ ነው ተብሏል፡፡

ዓለም አቀፍ ስታንደርድ ያሟላ፤ የአየር ማቀዝቀዣ የተገጠመለት የባቡር ጣቢያው 116 ነጥብ 8 ሚሊየን አሜሪካ ዶላር ወጪ ተደርጎበታል ነው የተባለው፡፡

ጣቢያው ለትራፊክ መጨናነቅ መፍትሄ ይሰጣል ተብሎ ታምኖበታል፡፡

ሶስት ደረጃዎች ያሉት ሲሆን÷ 225 ሜትር ርዝመት፣ 22 ሜትር ስፋት እና 28 ሜትር ጥልቀት አለው ነው የተባለው፡፡

8 መግቢያ እና መውጫ በሮች፣ 17 ኢስካሌተርስ እና አራት ሊፍቶችም ተገጥመውለታል ተብሏል፡፡

 

ምንጭ፡- ሲ ጂ ቲ ኤን አፍሪካ

Exit mobile version