Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

“ኢትዮጵያ ታምርት ” በሚል መሪ ቃል የኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት አምራቾችን አቅም የማሳደገያ ንቅናቄ መድረክ  እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)  “ኢትዮጵያ ታምርት ” በሚል መሪ ቃል የአዲስ አበባ የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት አምራቾችን አቅም የማሳደገያ የምክክርና ንቅናቄ መድረክ  እየተካሄደ ነው ።

መድረኩን በይፋ ያስጀመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ አብዛኛው የሀገራችን ዜጎች አምራች እድሜ ላይ የሚገኙ በመሆኑ ተባብረን ሰርተን በአጭር ግዜ የብልፅግና ማማ ላይ እንደርሳለን ብለዋል።

የዜጎችን ኑሮ ማሻሻልና የከተሞችን የስራ እድል ፈጠራን ለማሳደግ  የሚያስችሉ ፖሊሲዎችን ቀርፀን ወደስራ ገብተናልም  ነው  ያሉት።

የአዲስ አበባ ከተማ  ምክትል ከንቲባና የስራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊው  አቶ ጃንጥራር አባይ፥ በከተማችን ከተያዘው  እቅድ አንዱ ኢትዮጵያ ታምርት የሚለው ንቅናቄ አንዱ መሆኑን አንስተው በዚህም  ከዘርፉ በአመት ከፍ ለማድረግ ይረዳል ብለዋል።

በተጨማሪም የዛሬው  ንቅናቄ አሁን ላይ ካሉን  10 ሺህ 500 አምራች ኢንዱስትሪዎችን ቁጥር ወደ 22 ሺህ ለማሳደግም እንደሚረዳ ነው የጠቆሙት።

በተጨማሪም  ያለ ኢንዱስትሪ ልማት ያደገ ሀገር አለመኖሩን ያነሱት አቶ ጃንጥራር አባይ፥ “እኛም እንደ ሀገር ለመበልፀግ የተለያዩ ፖሊሲዎችን አሻሽለን ከኢንዱስትሪያሊስቶች ጋር ተቀራርበን መስራት አለብን” ብለዋል።

 

 

በዓለምሰገድ አሳዬ

Exit mobile version