ዓለምአቀፋዊ ዜና

ሰሜን ኮሪያ ሁለት ሚሳኤሎች አስወነጨፈች

By Tibebu Kebede

March 02, 2020

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 23 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሜን ኮሪያ ሁለት ሚሳኤሎች ማስወንጨፏን የሃገሪቱ ጦር አስታወቀ።

ሚሳኤሎቹ ከሃገሪቱ ምስራቃዊ የባህር ዳርቻ ወደ ጃፓን ባህር የተወነጨፉ ናቸው።

የአሁኑ ሙከራ የፈረንጆቹ 2020 ከገባ በኋላ የመጀመሪያዋ ሲሆን፥ ባለፈው ህዳር ወር ላይ ተመሳሳይ ሙከራ ማድረጓ ይታወሳል።

ዛሬ የተሞከሩት ሚሳኤሎች አጭር ርቀት ተወንጫፊ ሳይሆኑ እንደማይቀር የሃገሪቱ የጦር ሃይሎች የጋራ ምክር ቤት አስታውቋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision