Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ቻይና ጥልቀት በሌለው ውሃ ላይ መንሳፈፍ የሚችል ግዙፍ መርከብ ይፋ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ጥልቀት በሌለው ውሃ ላይ መንሳፈፍ የሚችል በዓለም አቀፍ ደረጃ ግዙፉ የተባለ መርከብ መስራቷን አስታውቃለች፡፡

ጥልቀት በሌለው ውሃ ላይ በተለዋዋጭ እንቅስቃሴ መንሳፈፍ የሚችለው ይህ ግዙፍ መርከብ በቻይና ጂኦፊዚካል ቢሮ የተሰራ ሲሆን÷ በሊያኦኒንግ ግዛት ዳሊያን ከተማ የተሳካ ሙከራውን አድርጓል፡፡

ግዙፉ መርከብ የዲጃታል ቁጥጥር ስርዓት የተገጠመለት እና የመሬት አሰሳ ማድረግ፣የመሬት መንቀጥቀጥ የሚከሰት ከሆነ የማስጠንቀቂያ መልዕክት ማድረስ እና የመስቀለኛ ቦታ አቀማመጥን መለየት የሚችል አቅም አለው ተብሏል፡፡

በዓለም ላይ ጥልቅ ባልሆነ ባህር ላይ መንሳፈፍ የሚችለው ይህ መርከብ ÷የ 5 ሜትር ጥልቀት ባለው ውሃ ላይ መንሳፈፍ የሚችል እና እስከ 40 ሜትር ጥልቅ ባህር መንሳፈፍ እንደሚችልም ተመላክቷል፡፡

የመርከቡ አሰራር የተለያዩ የመርከብ ዘመቻ ፍላጎቶችን የሚያሟላ እና በተለያዩ የባህር ዳርቻዎች ላይ አሰሳ ለማድረግ ተስማሚ ስለመሆኑ ሲጅቲኤን በዘገባው አመላክቷል፡፡

 

 

Exit mobile version