አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ20ኛ ሣምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ዛሬ በተደረገ ጨዋታ ፋሲል ከነማ አርባ ምንጭ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡
በአዳማ ሣይንስ እና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ በተደረገው ጨዋታ÷ ፋሲል ከነማ በበዛብህ መለዮ ድንቅ ጎል አርባምንጭ ከተማን በማሸነፍ ወሳኝ 3 ነጥብ ይዞ መውጣት ችሏል፡፡
አጼዎቹ ዛሬ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ወላይታ ዲቻን በግብ ክፍያ በመብለጥ 3ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ÷ አዞዎቹ ደግሞ በ26 ነጥብ በነበሩበት 7ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!