አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “የትንሳኤው ትርጉም በራሳችን ላይ ለውጥ እንዲያመጣ መፍቀድ አለብን” ሲሉ የአዲስ አበባ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ይህን ያሉት የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት የትንሳኤ በዓልን በአዲስ አበባ ስታዲየም ባከበሩበት ወቅት ነው፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግርም “የትንሳኤው ትርጉም በራሳችን ላይ ለውጥ እንዲያመጣ መፍቀድ አለብን” ብለዋል።
አክለውም “በትንሹ ፍቅርን በማካፈል፣ ሁሉን ሰው ሳናዳላ በእኩል ዓይን በመመልከት በፍትሐዊነት በማገልገል፣ በይቅር ባይነት ብንበደል እንኳን በምሕረት በማለፍ፣ ሌሎችን በመውደድ የትንሳኤውን ትርጉም በተግባር እንቀይር ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል”፡፡
ኢትዮጵያውያን በመካሰስና ጣት በመጠቋቆም ተራርቀንና ተነጣጥለን ልናሸንፍ እና አንዱ ተጎድቶ ሌሎቻችን ልንጠቀም አንችልም ማለታቸውን ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አንዱ አዝኖ ሌሎቻችን ልንደሰት እንደማንችል በመረዳት ልክ እንደ አንድ ቤተሰብ የጋራ ጉዳያችን እና ጥቅሞቻችን የተሳሰሩ ስለሆኑ ተከባብረን እየተሳሰብን በጋራ እንስራ ብለዋል በንግግራቸው፡፡
የወንጌል አማኞች ኅብረት ፕሬዚዳንት መጋቢ ፃዲቁ አብዶ በበኩላቸው÷ “ትንሳኤ መከራን፣ ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ እና ጨለማን ተሻግሮ ወደ አዲስና የሚደነቅ ብርሃን መግባትን እንዲሁም በአሸናፊነት መውጣትን የሚያመለክት የድል ብስራት ነው” ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!