የሀገር ውስጥ ዜና

የፋሲካ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው

By Mekoya Hailemariam

April 24, 2022

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፋሲካ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ይገኛል።

ፋሲካን በማስመልከት የሃይማኖት አባቶች ባስተላለፉት መልዕክት “የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓልን ስናከብር አንድነታችንን በማጠናከር እና የኢትዮጵያን ዘላቂ ሠላም ለማስፈን በተግባር በመስራት ሊሆን ይገባል” ብለዋል፡፡

“የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ የሰው ልጅ ሃጥያት የተሰረየበት ፣ ፍቅር የተገኘበት እንዲሁም እንዲሁም ደህንነት የተጎናፀፈበት ነው” ብለዋል፡፡

በዓሉን በተለያየ ምክንያት ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን በመደገፍ እና በመንከባከብ ማሳለፍ እንደሚገባም የሃይማኖት አባቶቹ አሳስበዋል፡፡

ህዝበ ክርስቲያኑም በመላ ሀገሪቱ ሠላም እንዲሰፍን ጥረቱን እንዲያጠናክር የሃይማኖት አባቶቹ ጠይቀዋል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ! ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!