አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ብዙዎች አገራችንን ለማገልገል እና ታላቋን ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ ሲሉ መሥዋዕትነት ከፍለዋል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ÷ ዛሬ ከጀግኖች የማዕከላዊ ዕዝ ብሔራዊ ኃይላችን አባላት ጋር ጊዜ በማሳለፌ ክብር ይሰማኛል ብለዋል፡፡
ብዙዎች ሀገራችንን ለማገልገል እና ታላቋን ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ ሲሉ መሥዋዕትነት ከፍለዋል ሲሉም ገልጸዋል፡፡
መሥዋዕትነት፣ ትጋት፣ ዕውቀት፣ ርኅራኄ እና አንድነት ሀገራችንን ልትደርስበት ወደሚገባት ከፍታ ያሻግሯታል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!