አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ኤች አር 6600” እና “ኤስ 3199” ረቂቅ ሕጎችን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በኒው ጀርሲ ግዛት ተካሄደ፡፡
በትናትናው ዕለት በ “ኤስ 3199” ረቂቅ ሕግ አርቃቂ ሴናተር ሮበርት ሜኔንዴዝ (ኒው ጀርሲ) ቢሮ ፊት ለፊት በተከናወነው ሰልፍ ላይ “ረቂቅ ሕጎቹ ኢትዮጵያንና ኤርትራን የሚጎዱ ናቸው”፣ ”ማዕቀብ ይገድላል ማዕቀብ ምንም አይቀይርም”፣ “ኤች አር 6600” እና “ኤስ 3199” ይሰረዙ እና “ሕጎቹ የኢትዮጵያና አሜሪካን ግንኙነት” የሚጎዱ ናቸው” የሚሉ መልዕክቶች ተላልፈዋል።
“ሮበርት ሜኔንዴዝ ሽብርተኞችን መደገፍ ያቁሙ”፣ “ሜኔንዴዝ ያረቀቁት ሕግ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያንን የሚጎዳ ነው”፣ “በሴኔት ምርጫው ለሮበርት ሜኔንዴዝ ድምጽ አንሰጥም” እና “የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በሚጎዳ ተግባር የሚንቀሳቀሱ የአሜሪካ ባለስልጣናትን በምርጫው በድምጽ መቅጣት አለብን” ሲሉ ሰልፈኞቹ መግለጻቸውን ኢዜአ ከኒው ዮርክ ኒው ጀርዚ ተስፋ ለኢትዮጵያ ድርጅት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
በኒው ጀርሲ፣ኮኔቲከት፣ፊላደልፊያና ኒው ዮርክ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ኤርትራውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በሰልፉ ላይ መሳተፋቸው ተገልጿል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!