Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኮንሶ ዞን ካራት ዙሪያ ወረዳ የወርቅ ማዕድን ቁፋሮ ሥራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮንሶ ዞን ካራት ዙሪያ ወረዳ ሌሃይቴ ቀበሌ የወርቅ ማዕድን ቁፋሮ ሥራ በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል፡፡
የቁፋሮ ሥራው÷ የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ገልገሎ ገልሾን ጨምሮ የዞኑ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ተጀምሯል፡፡
በወረዳው በወርቅ ማዕድን ቁፋሮ ዘርፍ 100 ሥራ አጥ ወጣቶች በመደራጀት በተሰጣቸው ፈቃድ መሰረት ሥራ መጀመራቸው ተመላክቷል፡፡
አካባቢው በጂ ፒ ኤስ ዳታ ተለይቶ በተጠናው መሰረት የወርቅ ክምችቱ ሊገኝ ይችላል በተባለበት 8 ሄክታር መሬት ላይ ሥራ መጀመሩ ነው የተገለጸው፡፡
የወርቅ ማዕድኑ ለአካባቢው ወጣት የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባሻገር ለዞኑ፣ ለክልሉ እና ለሀገር ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ እንደሚሆን መገለፁን ከኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version