አዲስ አበባ ፣ የካቲት 21 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው ለ30 የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አይነ ስውራን ተማሪዎች የላፕቶፕ ስጦታ አበረከቱ።
ስጦታው ከተበረከተላቸው ተማሪዎች መካከል 12ቱ ሴቶች ሲሆኑ 18ቱ ደግሞ ወንዶች ናቸው።
ላፕቶፖቹ ተማሪዎቹን በመማር ማስተማሩ ሂደት በተሻለ ሁኔታ ለማገዝ የሚረዱ ናቸው ተብሏል።
ወይዘሮ ዝናሽ ስጦታውን ባበረከቱበት ወቅት ተማሪዎቹ በትምህርታቸው የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ አበረታተዋቸዋል።
በፍሬህይዎት ሰፊው
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision