የሀገር ውስጥ ዜና

በደቡብ ክልል ከ11 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጠ

By Feven Bishaw

April 18, 2022

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) ከ11 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ 244 የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱን የደቡብ ክልል ኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ቢሮ አስታወቀ፡፡

በ2014 ዓ.ም ዘጠኝ ወራት በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ወደ ክልሉ ገብተው ኢንቨስት ለማድረግ ጥያቄ ያቀረቡና 11 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 244 ባለሃብቶች ወደ ስራ መግባት የሚያስችላቸውን ቅድመ ሁኔታ አሟልተው ከክልሉ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጥቷቸዋል ነው የተባለው፡፡