Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኮሮና ቫይረስ ምልክት ታይቶበታል በሚል በመለያ ማዕከል ገብቶ የነበረው ግለሰብ ከቫይረሱ ነጻ መሆኑ ተረጋገጠ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኮሮና ቫይረስ ምልክት ታይቶበታል በሚል በመለያ ማዕከል ገብቶ የነበረው ግለሰብ ከበሽታው ነጻ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ተጠርጣሪው ከአምስት ቀን በፊት ከቻይና ቤጂንግ ወደ ኢትዮጵያ የመጣ ሲሆን፥ የኮሮና ቫይረስ ምልክት ታይቶበታል በሚል ወደ ማቆያ ማዕከል እንደገባ ትናንት ሚኒስቴሩ አስታውቆ ነበር።

በማቆያ ማዕከሉም ተለይቶ ክትትል ከተደረገለት በኋላ ናሙና ተወስዶ በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ላቦራቶሪ ተሰርቶለታል።

በላቦራቶሪ ምርመራ ውጤት መሰረትም ግለሰቡ ከቫይረሱ ነጻ መሆኑ ተረጋግጧል ብሏል ሚኒስቴሩ።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

Exit mobile version