Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ሰላምን የሚሰብከው ወጣት

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 20፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ሶሪያውያን ስደተኞችን ከተመለከተ በኋላ በመዲናዋ ጎዳናዎች ስለሰላም የሚሰብከው ወጣት የበርካቶችን ትኩረት ስቧል።

ሰይፉ አማኑኤል የተባለው የታክሲ አሽከርካሪ በተጨናነቁ የአዲስ አበባ ጎዳናዎች መሃል፥ የሰላምን አስፈላጊነት በተለያዩ መንገዶች እያስተላለፈ ይገኛል።

ወጣቱ ሀሳቡ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ሶሪያውያን ስደተኞች እጃቸው እርዳታ ፍለጋ ሲዘረጉ ከተመለከተ በኋላ እንደመጣለት ይናገራል።

ሶሪያውን ስደተኞች አሁን ከገቡበት ችግር በፊት ከነበራቸው ህይወት ወጥተው አሁን ላይ በአዲስ አበባ ጎዳና ላይ እጃቸውን ለእርዳታ እንዲዘረጉ ያደረጋቸው የሰላም እጦት መሆኑን ጠቁሟል።

በዚህ ተግባሩ የተወሰኑ ሰዎች ቢስቁበትም ሰላምን በመስበኩ የሚያገኘው ደስታ ከፍ ያለ መሆኑንም ነው የሚናገረው።

“ሰላም ሳይኖር ማንኛውም ነገር ቢኖርህ፤ ብትይዝ ምንም አታደርገውም” ሲል የሰላምን አስፈላጊነት ገልጿል።

ታክሲ በማሽከርከር የሚተዳደረው ሰይፉ በየቀኑ ስለሰላም በሶስት ሰዎች ላይ ግንዛቤ መፍጠር መቻል ትልቅ ደስታ እንደሚሰጠውም ተናግሯል።

በዚህ ተግባራ በየዕለቱ ማሳለፈው ጊዜ እንደባከነ አልቆጥረውም ነው ያለው።

ምንጭ፡- ቢቢሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

Exit mobile version