አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጥላ ሥር የሚንቀሳቀሰው የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስተባባሪነት 47 የሰብዓዊ ዕርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ክልል እየተጓዙ መሆኑን ድርጅቱ ገለፀ፡፡
እየተጓጓዘ ያለው የሰብዓዊ ዕርዳታም ÷ ምግብ፣ ዓልሚ ምግቦችን እና ሌሎች ሕይወት አድን ቁሳቁሶችን እንዳካተተ ነው የዓለም ምግብ ፕሮግራም ያስታወቀው።
ከምግብ እና መሰል አቅርቦቶች በተጨማሪ 3 የነዳጅ ቦቴዎች በማጓጓዝ ሂደቱ ለተሸከርካሪዎቹ ለጥቅም እንዲውሉ ታስቦ አብረው ወደ ትግራይ ክልል እየተንቀሳቀሱ እንደሆነም ነው ድርጅቱ በትዊተር ገጹ ያመላከተው፡፡