አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያቀርቧቸውን አቤቱታዎች ቡድን በማዋቀር የማጣራት ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እያካሔደ ነው።
የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሚያቀርቧቸው አቤቱታዎች የምርመራ ቡድን በማደራጀት በርካታ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን ቦርዱ ገልጿል።
በመድረኩ የፓርቲዎቹን አቤቱታ እንደመነሻ በመያዝ አቤቱታው የቀረበባቸው አካባቢዎች ድረስ በመንቀሳቀስና በማጣራት ህጋዊ መፍትሔ እንዲኖረው አድርጓል።
እንደ አብነት በኦነግ እና ኦፌኮ ፓርቲዎች በኩል የተነሱትን አቤቱታዎች በመያዝ ወደ ኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ቦታዎቹ በመንቀሳቀስ የምርመራና ማጣራት ስራ መከናወኑ ተገልጿል።
በዚህም ህጋዊ አሰራር እንዲተገበር ውሳኔ አስተላልፎ መፍትሄ ማሰጠቱን በቦርዱ በቀረበው ሪፖርት ተመልክቷል።
በአጠቃላይ በተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚቀርቡ አቤቱታዎችን ምላሽና መፍትሄ ለመስጠት ምርጫ ቦርድ ሰባት አጣሪ ቡድኖችን አዋቅሮ ሲሰራ ቆይቷል ተብሏል።
ለበርካታ ወራት ሲያከናወን የቆየው የአቤቱታ ማጣራትና የምርመራ ስራ የተጠናቀቀ መሆኑን በመጠቆም በሌላ ጊዜም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ተመሣሣይ ኮሚቴዎች ሊዋቀሩ ይችላሉ ተብሏል።
በዛሬው የውይይቱ መድረክ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከአባላቶቻቸው፣ ከመንግሥት እና ከተለያዩ ምንጮች የሚያገኙትን ገንዘብ እንዴት ማስተዳደር ይኖርባቸዋል በሚለው ጉዳይ ላይ ምክክር እንደሚደረግ ይጠበቃል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!