የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በደቡብ አፍሪካ የጎርፍ አደጋ ባደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ

By Melaku Gedif

April 14, 2022

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በደቡብ አፍሪካ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ ምክንያት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ።

በሀገሪቱ የወደብ ከተማ ደርባን  የጣለው ከባድ ዝናብ በአካባቢው የጎርፍ አደጋን አስከትሏል።

በዚህም አደጋ ምክንያት ከ300 በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስተውቀዋል።

በተጨማሪም አደጋው በአካባቢው በሚገኝ መሰረተ ልማት ላይ ጉዳት አድርሷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ  እና በአደጋው ለተጎዱ ደቡብ አፍሪካውያን ባስተላለፉት መልዕክት÷ በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ኢትዮጵያ በአጋርነት አብራቸው እንደምትቆም አረጋግጠዋል።