Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አሸባሪው ህወሓት በፈጸመው ወረራ በትራንስፖርት መሠረተ ልማቶች ላይ ከ1 ነጥብ 75 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ውድመት አድርሷል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በአማራ እና አፋር ክልሎች በፈጸመው ወረራ በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት መስጫ ተቋማትና መሰረተ ልማቶች ላይ ከ1 ነጥብ 75 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ውድመት ማድረሱን ጥናት አመላከተ፡፡
 
በአማራ እና አፋር ክልሎች ህወሓት በፈጸመው ጥቃት የደረሰው ጉዳት የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በሠራው ጥናት ላይ የዘርፉ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ተወያይተዋል፡፡
 
የትራንስፖርትእና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በርኦ ሀሰን÷ በጥናቱ ላይ ውይይት መደረጉ ከተሳታፊዎች ተጨማሪ ግብዓት ለመሰብሰብ እና በዘርፉ ላይ በቀጣይ በሚደርሱ ተጽዕኖች እና ጫናዎች ላይ በምን አግባብ መፍታት እንዳለብን ለመዘጋጀት ያለመ ነው ብለዋል፡፡
 
በአማራ ክልል በአሽባሪው ቡድን ወረራ ከተፈጸመባው ዞኖች መካከል በሰሜን ሸዋ፣ በኦሮሚያ ልዩ ዞን፣ በደቡብ ወሎ፣ በደሴ ከተማ አስተዳደር፣ በሰሜን ወሎ፣ በደቡብ ጎንደር ፣በሰሜን ጎንደር እና ዋግኸምራ ዞን ስር በሚገኙ ወረዳዎች መካከል ባሉ 12 ወረዳዎች ላይ የጥናት ቡድኑ መረጃዎችን ማሰባሰቡ ም ተመላክቷል፡፡
 
በዚህም የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ በቢሮ ቁሳቁሶች፣ በግንባታ ዕቃዎች፣ በጽህፈት መሳሪያዎች ፣በማሽነሪ እና ተሽከርካሪዎች እና በመንገድ መሰረተ ልማት በድምሩ 1 ቢሊየን 344 ሚሊየን 717 ሺህ 276 ብር የሚገመት ንብረት ላይ ውድመትና ዘረፋ መፈጸሙ ነው የተገለጸው፡፡
 
በተመሳሳይ በአፋር ክልል በ3 ዞኖች በተሰበሰበ መረጃ መሰረት በትራንስፖርት በአገልግሎት መሰጫ ተቋማትና መሰረተ ልማት በወደሙ እና በተዘረፉ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ በቢሮ ቁሳቁሶች፣ በግንባታ ዕቃዎች፣ በጽህፈት መሳሪያዎች፣ በማሽነሪ እና ተሽከርካሪዎች በመንገድ መሰረተ ልማት ላይ በድምሩ 406 ሚሊየን 69 ሺህ 625 ብር የሚገመት ንብረት መውደሙና መዘረፉ ተመላክቷል፡፡
 
ኅብረተሰቡን ባሳተፈው ውይይትም የልማትና የመልካም አሰተዳደር ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን ግብረ-መልስ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
 
በቀጣይ ዕቅድ ላይም ውይይት ተደርጎ አቅጣጫ መቀመጡን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
Exit mobile version