አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ወሎ ዞን ቦረና ወረዳ በህገ-ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ 1 ሚሊየን 80 ሺህ ብር የሚወጣ 120 ፋልኮል ሽጉጥ መያዙን የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት ተወካይ ምክትል ኢንስፔክተር ኡስማን ሰይድ ፥ ከብሔረዊ መረጀና ደህንነት በደረሰ ጥቆማ መሠረት መነሻውን ከሰሜን ጎንደር ያደረገ አንድ ኮብራ መኪና 120 ፋልኮል ሽጉጦችን ጭኖ ወደ ኮምቦልቻ ሲጓዝ በቦረና ወረዳ ከሌሊቱ 6:00 ሰዓት ላይ መያዙን ገልጸዋል።
ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ምክትል ኢንስፔክተሩ ተናግረዋል፡፡
ህብረተሰቡ መሰል የህገ ወጥ ተግባራት ሲመለከት ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበር ጥሪ መቅረቡንም ከወረዳው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!