Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በቤልጂየም ’ኤች አር 6600’ እና ‘ኤስ 3199’ ረቂቅ ሕጎችን በመቃወም ሰልፍ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ላይ ኢፍትሃዊ ጫና የማድረግ ዓላማ ያላቸውን ’ኤችአር 6600’ እና ‘ኤስ 3199’ ረቂቅ ህጎች በመቃወም በቤልጂየም የአሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ።

ሰልፈኞቹ የአሜሪካ ህዝብ ጨምሮ ዓለም ዓቀፍ ተቋማት ከኢትዮጵያ ጎን እንዲሰለፉም ጠይቀዋል።

ኢትዮጵያውያኑ አሸባሪው የህወሓት ቡድን በአፋር እና አማራ ክልሎች የተለያዩ ቦታዎች ላይ የደረሰውን ግፍ እና በደል በመገንዘብ የተወሰኑ የአሜሪካ ኮንግረስ እና ሴኔት አባላት ያረቀቋቸውን ህጎች እንዲሰርዙ የሚጠይቁ መፈክሮችን አሰምተዋል።

ሰልፈኞቹ ከአሜሪካ መንግስት በተጨማሪም ሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት በመሬት ላይ ያለውን ሐቅ በመገንዘብ ከኢትዮጵያውያን ጎን እንዲሰለፉም ጥሪ ማቅረባቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

በቤልጂየም የተካሄደው ሰልፍ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ኤፍሬም ምትኩ ፥ ዲያስፖራው የሚያድርጋቸው እንዲህ ያሉ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version