የሀገር ውስጥ ዜና

በቅርቡ የተሾሙ አምባሳደሮች በተመደቡበት ሀገር የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲያስተዋውቁ ተጠየቁ

By Meseret Awoke

April 12, 2022

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቅርቡ አዲስ የተሾሙ አምባሳደሮች በተመደቡባቸው ሀገራት በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲያስተዋውቁ የሚያግዝ ጉብኝት ተካሂዷል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ፥ በቅርቡ ሹመት ለተሰጣቸው አምባሳደሮች ቦሌ ለሚ፣ ቂሊንጦና አዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን አስጎብኝቷል፡፡

በተለያዩ ሀገራት የተሾሙ አምባሳደሮች በኢትዮጵያ በተለይም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያሉ ዝርዝር የኢንቨስትመንት አማራጮችን ተመልክተው በሚሄዱባቸው ሀገራት በማስተዋወቅ ኢንቨስትመንትን ወደ ኢትዮጵያ ለመሳብ እንጂችሉ ያለመ ጉብኝ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ÷ አምባሳደሮች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለአለም ለማስተዋወቅ መስራት አለባቸው ብለዋል።

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያሉ የስራ እንቅስቃሴዎችን፣ የኢንቨስትመንት አማራጮችን እና የወደፊት ስራዎች ላይ ዝርዝር ማብራሪያና ገላጻ ተደርጓል፡፡

አምባሳደሮቹ በበኩላቸው÷ ጉብኝቱበኢንዱስትሪ ፓርኮች ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለአለም ለማስተዋወቅ እንደሚረዳቸው መናገራቸውን ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!