አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአገልግሎት አሰጣጡ ምቹና ተመራጭ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው ገለጹ፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴር ተግባራዊ ለማድረግ እያስጠና ያለውን መሰረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ አስመልክቶ ከዋናው መስሪያ ቤትና ከቅርንጫፍ ጽፈት ቤቶች ለተወጣጡ አመራሮችና ሰራተኞች ለአምሥት ቀናት የሚቆይ ሥልጠና እየሰጠ ነው፡፡
በሥልጠናው ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያለው ÷ “እየተጠና ያለውን መሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ ተግባራዊ በማድረግ እና ለግብር ከፋዮች ዘመናዊ፣ ምቹ እና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ተቋማችንን በሀገርና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመራጭ እንዲሆን ማድረግ ይገባናል” ብለዋል፡፡
የታክስ አሰራሩን ለማዘመንም እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙትሚኒስትሩ ÷ ሁሉም የተቋሙ አመራርና ሰራተኞች ከአድሎአዊ አሰራር ነፃ ሆነው የሚጠበቅባቸውን ስራ በተገቢው ሁኔታ በመስራት ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን የታክስ ገቢ በትክክል መሰብሰብ እንደሚገባቸው መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!