Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የዓለም ማህበረሰብ ወደ ቅዱስ ላሊበላ ቅርስ እንዲመለከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ወደ ቅዱስ ላሊበላ ዓለም አቀፍ ቅርስ እንዲመለከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ ጥሪ አቀረቡ፡፡

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እና በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በነበረው ጦርነት የቅዱስ ላሊበላ ቅርስ የቱሪዝም እና የከተማው እንቅስቃሴ ከፍተኛ ጫና ውስጥ መውደቁን ገልጸዋል።
የችግሩን ስፋት እና ጥልቀት በመገንዘብ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለድጋፍ እጁን እንዲዘረጋም ጥሪ አቅርበዋል::

የቅዱስ ላሊበላ ዓለም አቀፍ ቅርስ ለኢትዮጵያ ሐብት ፣ ለሕዝቧም ኩራት፣ ለቤተ ክርስቲያኗም ከፍተኛ የመንፈሳዊ ጥበብ ውጤትና መገለጫ በመሆኑ መንግስትን ጨምሮ ሌሎች መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ችግሩን ለመቅረፍ ሊረባረቡ ይገባል ብለዋል::

በገዳሙ የውስጥ ገቢ ተጀምሮ የነበረው የቅርስ ልማት ማለትም የመካነ ቅርሱ አጥርና በር፣ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች፣ የመሬት ማስተካከልና የዛፍ ተከላ፣ ከአብያተ ክርስቲያናቱ ጋር እኩል ዘመን ያላቸውና በባሕላዊ አቀማመጥ ችግር እየደረሰባቸው ያሉ ተንቀሳቃሽ ቅርሶች፣ እንቁ፣ ከወርቅ፣ ከብር፣ ከነሐስ፣ ከመዳብ፣ ከብረት፣ ከድንጋይ፣ ከሸክላ፣ ከእንጨት፣ ከቆዳ እና ሌሎች ማዕድናት የተሠሩ ቅርሶቸ ማስቀመጫ ደረጃውን የጠበቀ ቤተ መዛግብት (ዘመናዊ ሙዚየም) ግንባታ ለማስፈፀም ከአቅም በላይ በመሆኑ የድርሻችን በመወጣት ቅርሳችን እንጠብቅ የሚል መልዕክት በጊዜያዊ የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴው ተላልፏል፡፡

የባንክ ሂሳብ ቁጥር ፡- በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ አቢሲኒያና ዳሽን ባንኮች በ0712 የባንክ የሂሳብ ቁጥር ለቅዱስ ላሊበላ ገዳም ዓለም አቀፍ ቅርስ ዜጎች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0911061164 እና 0913912457 መደወል እንደሚቻል ተገልጿል፡፡

በአዲሱ ሙሉነህ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version