የሀገር ውስጥ ዜና

በመተከል ዞን ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታወቀ

By Meseret Awoke

April 12, 2022

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመተከል ዞን በተለያዩ መጠለያ ጣቢዎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች 5ኛው ዙር ሰብዓዊ ድጋፍ በመቅረብ ላይ መሆኑን የክልሉ አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

በዞኑ በተፈጠረው አለመረጋጋት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ 282 ሺህ የሚደርሱ ዜጎች የሚደረገው ሰብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

ኮሚሽኑ ከብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ጋር በመተባበር የተጠየቀው ከ42 ሺህ 300 ኩንታል በላይ የሰብዓዊ ድጋፍ በአሁኑ ሰዓት ለተፈናቃዮች እየቀረበ መሆኑን በኮሚሽኑ የምላሽ ፍላጎትና እርዳታ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ዘውዱ ተሾመ አስታውቀዋል።

እስካሁን በዞኑ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው የሚገኙ 282 ሺህ የሚደርሱ የህብረተሰብ ክፍሎች በየወረዳ ባለው መጠለያ ጣቢያ እንደሚገኙ ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

በ5ኛው ዙር የሰብዓዊ ድጋፍ በዞኑ ስር በሚገኙ በሁሉም ወረዳዎች በመጓጓዝ ላይ መሆኑን ኮሚሽኑ ማስታወቁን ከቤንሻንጉል ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!