አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የእስራኤል የልዑካን ቡድን በአማራ ክልል በአሸባሪው ሕወሓት ጉዳት የደረሰባቸውን የጤና ተቋማት መልሶ ለመገንባት እና ድጋፍ ለማድረግ ጎንደር ገብቷል።
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የወደሙ የጤና ተቋማትን መልሶ መገንባት ላይ ያተኮረ ውይይት እንደሚካሄድ መገለጹን ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ያገኘነው መረጃ ያመላታል፡፡
ልዑካን ቡድኑ ጎንደር አፄ ቴዎድሮስ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በጤና ሚኒስቴር የእናቶችና ህጻናት ጤና ዳይሬክተር ዶክተር መሰረት ዘላለምን ጨምሮ፥ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር አስራት አፀደወይን እና ሌሎች የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የእስራኤል የሕክምና ቡድን አባላት በትናንትናው ዕለት ለሰብአዊ ተልዕኮ አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!