Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአማራ ክልል ተደራጅተው የመኖሪያ ቤት ለመገንባት ለሚጠብቁ ዜጎች መሬት ለመስጠት ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በህጋዊ መንገድ ተደራጅተው የመኖሪያ ቤት ለመገንባት ለሚጠብቁ ዜጎች መሬት ለመስጠት ዝግጅት መጠናቀቁን የአማራ ክልል ከተሞችና መሠረተ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ኃላፊ አቶ ቢያዝን እንኳሆነ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት ፥ ከዚህ በፊት በርካታ ማህበራት ተደራጅተው የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ እየጠበቁ ቢሆንም በተለያዩ መመሪያዎች አለመተግበር ምክንያት መጉላላት ተፈጥሯል።

በተለይም የባህር ዛፍ ካሳ አከፋፈል ላይ ከዚህ በፊት ህግ ባለመኖሩ ለማህበራት ቦታ ለማስተላለፍ ማነቆ እንደነበር ጠቅሰው ፥ በአሁኑ ወቅት ግን የካሳ አከፋፋሉ መመሪያ ተዘጋጅቶለት ጸድቆ ያለቀ በመሆኑ የቤት መስሪያ ቦታ የሚጠባበቁ ማህበራት በቀጣይ ጊዜያት ቦታ ይሰጣቸዋል ነው የተባለው።

በባህር ዳር እና አካባቢዋ የመሬት ሽንሸና እየተጠናቀቀ መሆኑን ያነሱት ኃላፊው ፥ በቀጣይ ሌሎች አካባቢዎችም ወደ ተግባር ይገባሉ ብለዋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ህገ ወጥ የቤት ማህበራትን በማጋለጥ የሚገባው አካል ብቻ እንዲያገኝ በማድረጉ በኩል ማህበረሰቡ ኃላፊነቱን እንዲወጣም ጥሪ ቀርቧል።

በከድር መሃመድ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version