የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነትን በሚመለከት ከሱዳኑ አቻቸው ጋር ተወያዩ

By Meseret Awoke

April 11, 2022

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአልጀሪያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በአልጀሪያ ከሱዳን አምባሳደር ኤልኦቤይድ መሃመድ ኤልኦቤይድ ጋር በኢትዮጵያና ሱዳን ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ ውይይት አድርገዋል።

በኢትዮጵያና ሱዳን ግንኙነት፣ በሕዳሴ ግድቡ እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ፣ በአህጉራዊና ዓለም ዓቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ውይይት እንደነበርም ተገልጿል።

ውይይቱ ጠቃሚ የሃሳብ ልውውጥ የተደረገበት መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!