Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከ108 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ108 ሚሊየን 214 ሺህ ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢና የወጪ የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን ባለፈው ሳምንት ባደረገው ክትትል 99 ሚሊየን 386 ሺህ ብር የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና 8 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የወጪ የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ተይዘዋል፡፡

የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት ድሬድዋ ፣ አዲስ አበባ ኤርፖርት እና ጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች መሆናቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች ፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በበረራና በጥቆማ የተያዙ ሲሆን ፥ የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋዉሩ የተገኙ 11 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ቡና፣ መድሃኒት፣ ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ እቃዎች ፣የጦር መሳሪያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች እና የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድን ለመግታት ሁሉም ባለድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣም ጥሪ ቀርቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version