Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሆቴል መረጃዎችን ከጸጥታ ተቋማትጋር ማስተሳሰር የሚያስችል የመረጃ አስተዳደር ስርዓት ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጸጥታ ዘርፉን የመረጃ አያያዝ የሚያዘምን የፖሊስና ሆቴሎች የመረጃ አያያዝና አስተዳደር ስርዓት በዛሬው ዕለት ተመርቋል፡
 
ስርዓቱ የሆቴል መረጃዎች ከጸጥታ ተቋማት ጋር እንዲተሳሰሩ የሚያደርግና የፀጥታ ተቋማትን የመረጃ አያያዝ ዲጂታላይዝ ማድረግ የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል፡፡
 
በምረቃ ስነ ስርዓቱ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ÷ የዲጂታል የመረጃ አያያዝ ስርዓቱ የፀጥታ ተቋማትን አሰራር ቀልጣፋ በማድረግ ወንጀልን ቀድሞ ለመከላከል እንደሚያግዝ ተናግረዋል።
ስርዓቱ የመረጃ አያያዝን ከማዘመን ባለፈ በቂ አገራዊ የመረጃ ስብስብ እንዲኖር በማድረግ የትልቅ መረጃ ትንተና ላይ የራሱ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ብለዋል።
 
ስርዓቱን ያለማው የሊንክ ኦል ቴክኖሎጂ አክሲዮን ማህበር መስራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ የኑስ አብዱ አህመድ በበኩላቸው÷ ስርዓቱ በባለድርሻ አካላት ጥናትና ግምገማ ተደርጎበት ለምረቃ መብቃቱን ጠቁመዋል፡፡
 
ስርዓቱ ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎች፣ የሆቴል ባለንብረቶች፣ የፌደራል፣ የክልልና የከተማ አስተዳደር የፖሊስ ተቋማትን እንዲሁም የትራፊክ ፖሊስን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
 
ለፍትህ፣ ለቱሪዝም፣ ለሰብዓዊ መብት፣ ለሰላም ዘርፎች ጠቃሚ ግብዓቶችን የሚሰጥ መሆኑንም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
Exit mobile version