አዲስ አበባ፣መጋቢት 30፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከደቡብ ኮሪያ አቻቸዉ ኪም ዋን ጁንግ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸው አምባሳደር ሬድዋን ኢትዮጵያ ከደቡብ ኮሪያ ጋር ከአውሮፓውያኑ 1963 ጀምሮ የተጠበቀ ግንኙነት እንደነበራት አስታዉሰዋል።
ይህንን ዘመናትን የተሻገር የዲፕሎማሲ ግንኙነት አሁን ይበልጥ በማጠናከር ደቡብ ኮሪያ በኢትዮጵያ ዉስጥ ባለዉ ለዉጥ ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እና ድህነት ቅነሳ የመንግስት ተግባራት ድጋፍ እንድታደርግ ጠይቀዋል ።
ኢትዮጵያ እያከናወነች ባለዉ የለዉጥ አመታት ጉዞ ውስጥ ደቡብ ኮሪያዉያን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ባሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች እና እድሎች እንዲሳተፉም ነው ጥሪ ያቀረቡት።